ከዕንቁ መጽሔት የተወሰደ - ጸሐፊው በፍቅር ለይኩን፡፡
በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ጓደኞቿና የነፃነት ትግሉ አጋሮቿም፡- ‹‹እናዝናለን ኤሚ…ፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል…፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽ…ሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና
↧