ቤተክህነቱን እያመሱ የሚገኙትና በኪራይ ሰብሳቢ ተግባራቸው እጅና ጓንት የሆኑት ተስፋዬ ውብሸትና እስክንድር ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለማጋበስ አልመው የወጠኑትና እንቅስቃሴ የጀመሩበት ደብዳቤ ከበላይ አካል በተጻፈ ደብዳቤ መታገዱ ተሰማ፡፡ እስክንድርና ተስፋዬ «አትራፊ ስራ» ብለው በህዝብ ግንኙነት መምሪያው ስም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሕይወት ታሪክ ዙሪያ 112 ገጽ ጋዜጣና መጽሔት አዘጋጅተናልና እስፖንሰር ሁኑን ብለው ለስድስት አብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ ከጻፉና ገንዘብ ለመሰብሰብ አሰፍስፈው ባሉበት ሁኔታ በስማቸው ሊነገድ መሆኑን መረጃ የደረሳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ሃላፊ በብፁዕ
↧